ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ ቀጣይነት ባለዉ የስኬት ጉዞ ላይ!

ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ 6ኛ መደበኛ እና 2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ህዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም መገናኛ 24 አካባቢ በሚገኘው ኮከብ አዳራሽ አካሂዷል፡፡ ከተመሠረት ስድስት ዓመት ያሳለፈው ብርሃን ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተደራሽነቱን በማስፋት እና ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት በመስጠት በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ በፈጣን ዕድገት ላይ የሚገኝ ባንክ ነው፡፡

ባንኩ በተለያዩ የአፈፃፀም መለኪያዎች ከዓመት ወደ ዓመት ሁለንተናዊ እድገት እያሳየ የሚገኝ ሲሆን ይህም በአስተማማኝ የእድገት መሠረት ላይ የሚገኝና ቀጣይነት ያለው ዕድገት የሚያስመዘግብ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ እ.ኤ.አ ሰኔ 30 2015 በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የባንኩን አፈፃፀም በምንመለከትበት ጊዜ በበጀት ዓመቱ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ክምችት ብር 3.1 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ52.5 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡ የብድር ክምችቱን በተመለከተ ካለፈው ዓመት የ60.5 በመቶ እድገት በማሳየት ብር1.9 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው የበጀት ዓመት መጨረሻ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ካለፈው ዓመት የ48 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ብር 4.17 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን በካፒታል ረገድም ባንኩ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ. እስከ ሰኔ 30 2016 ባንኮች እንዲያሟሉ ያስቀመጠውን የብር 500 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል ግብ አስቀድሞ በማሟላት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የተከፈለ ካፒታሉን ወደ ብር 573 ሚሊዮን አሳድጓል፡፡

ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ከነበረበት ጉዳይ አንዱ ተደራሽነቱን የማስፋትና የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ሲሆን በዚህም በበጀት ዓመቱ 27 ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በመክፈት አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 72 አድርሷል፡፡ በሌላ በኩል የደንበኞቹን ቁጥር ለማሳደግ ከፍተኛ ሥራ በመስራት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የባንኩ አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 108,283 የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት የ82.9 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ባንኩ ተጨማሪ 488 ሠራተኞችን በመቅጠር በአጠቃላይ ለ1,181 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል፡፡



2 Comments

 • Mersha Ewnetu

  Dear BIB executives,

  Many thanks for your effectiveness and success that you brought to our Bank. But, would you please help us to know our dividends or profit every year with mobile or internet so that we can update ourselves timely. Since the bank is working centrally, it is difficult for regions shareholder to know their status timely. And also, most of the shareholders do not know how and when to collect the profit regularly.

  Regards!

  Mersha Ewnetu.
  Bahir Dar.

  • Admin

   Dear Mersha,

   That is a good and excellent looking regards to the bank future move.We will try to solve the problem as soon as possible.

   Regards,

   Administrator

Leave a Reply

Demos

Layout

Wide
Boxed
Scroll up